በሊባኖስ ቤሩት ወደብ አቅራብያ የደረሰው ፍንዳታ ያስከተለውን ጉዳት በምስል

ታትሟል

በቤይሩት ትናንት አመሻሽ ላይ ባጋጠመው ከባድ ፍንዳታ ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት እንደደረሰባቸው ተነግሯል።

በጎ ፈቃደኞች የትናንትናውን ፍንዳታ ተከትሎ የተሰባበሩ መስታወቶችን ሲያፀዱ
የምስሉ መግለጫ, በጎ ፈቃደኞች የትናንትናውን ፍንዳታ ተከትሎ የተሰባበሩ መስታወቶችን ሲያፀዱ
የቤይሩት ወደብ ሙሉ በሙሉ በፍንዳታው መውደሙ ተገልጿል
የምስሉ መግለጫ, የቤይሩት ወደብ በፍንዳታው በከፍተኛ ሁኔታ መውደሙ ተገልጿል
ትናንት በደረሰው ፍንዳታ የቤሩት አውራ ጎዳናዎች በፍርስራሶች ተሸፍነዋል
የምስሉ መግለጫ, ትናንት በደረሰው ፍንዳታ የቤሩት አውራ ጎዳናዎች በፍርስራሶች ተሸፍነዋል
በደረሰው ፍንዳታ የግለሰቦች ቤትም ፈራርሷል
የምስሉ መግለጫ, በደረሰው ፍንዳታ የግለሰቦች ቤትም ፈራርሷል
በቤሩት ለስደተኞች የቆመው ሃውልት በፈራረሱ ህንጻዎች መካከል ምንም ሳይሆን ቆሟል
የምስሉ መግለጫ, በቤሩት ለስደተኞች የቆመው ሃውልት በፈራረሱ ህንጻዎች መካከል ምንም ሳይሆን ቆሟል
በፍንዳታው ጉዳት የደረሰባትን ሴት አቅፎ የሚወስድ ግለሰብ
የምስሉ መግለጫ, በፍንዳታው ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል
በፍንዳታው የተጎዱ ህንጻዎች
የምስሉ መግለጫ, በፍንዳታው መስታወታቸው የረገፈ ህንጻዎች
ፍንዳታው በደረሰበት ወቅት በርካቶች ተደናግጠው በጎዳና ላይ ሲሯሯጡ ታይተዋል
የምስሉ መግለጫ, ፍንዳታው በደረሰበት ወቅት በርካቶች ተደናግጠው በጎዳና ላይ ሲሯሯጡ ታይተዋል
ፍንዳታው የደረሰው ሊባኖስ በኮሮናቫይረስና በምጣኔ ሃብት ድቀት በተጎዳችበት ወቅት ነው
የምስሉ መግለጫ, ፍንዳታው የደረሰው ሊባኖስ በኮሮናቫይረስና በምጣኔ ሃብት ድቀት በተጎዳችበት ወቅት ነው
በሊባኖስ የወደብ አቅራብያ የደረሰው ፍንዳታ ከመቶ በላይ ሰዎችን ህይወት ሲቀጥፍ በርካታ ህንጻዎች ላይ ጉዳት አድርሷል
የምስሉ መግለጫ, በሊባኖስ የወደብ አቅራብያ የደረሰው ፍንዳታ ከመቶ በላይ ሰዎችን ህይወት ሲቀጥፍ በርካታ ህንጻዎች ላይ ጉዳት አድርሷል
በፍንዳታው የተጎዱ ህንጻዎች
የምስሉ መግለጫ, በፍንዳታው የተጎዱ ህንጻዎች በከፊል