ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ታላላቅ ኮከቦች እና ነባር ተቀናቃኞች - በዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ምን ይጠበቃል?
የዓለም ዋንጫ አይረሴ አጋጣሚዎችን እያሳየ ቀጥሏል። ነገ ማክሰኞ በሚጀምረው ግማሽ ፍጻሜ የተፎካካሪዎቹ ብዛት ወደ አራት ወርዷል።
ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ እንግሊዝ እና አርጀንቲና የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮን ለመሆን የሚቀራቸው ሁለት ጨዋታዎችን ማሸነፍ ብቻ ነው። ወደ ፍጻሜው ለመደረስ የሚፎካከሩት እነዚህ ቡድኖች እዚህ ደረጃ ላይ ስህተት መስራት መቋቋም የሚችሉ አይመስልም።
በቀጣዩ የአራት ቡድኖች ፉክክር ምን ልንመለከት እንችላለን? ይህ ዘገባ በዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ምን እንደሚጠብቅ ያስረዳዎታል።
ምባፔ ከ ያማል - የአውሮፓ ኮከብ ተጫዋቾች ፍጥጫ
ምን ይጠበቃል? - ሁለቱ አውሮፓ ጠንካራ ቡድኖች የሚጫወቱበት ይህ ግጥሚያ ታላቅ የዓለም ዋንጫ ጨዋታ የመሆን እድል አለው።
ፈረንሳይ ሞሮኮን 2 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ ላይ የዘንድሮ ዓለም ዋንጫ ስምንተኛ ግቡን ያስቆጠረው ኪሊያን ምባፔ በድጋሚ መነጋገሪያ ሆኗል። ምባፔ በዓለም ዋንጫ ያስቆጠራቸው ግቦች ብዛት ክብረ ወሰኑን ከያዘው ሊዮኔል ሜሲ የሚያንሰው በአንድ ብቻ ነው።
ነገር ግን የፈረንሳይ ትልቁ ጥንካሬ ሜዳው ላይ ያላቸው ብቃት ነው። በሩብ ፍጻሜ ጨዋታ የመጨረሻዋን ግብ ያስቆጠረው ኡስማን ዴምቤሌም የግብ ብዛቱን ወደ አምስት አሳድጓል።
ማይክል ኦሊሴ በአንጻሩ ሜዳ ላይ የፈጠራ አቅሙን እያሳየ ሲሆን አምስት ግቦችን በማቀበል በቀዳሚነት ተቀምጧል።
ቢሆንም ግን ከሁለት ጊዜ የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ ስፔን ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ቀላል አይሆንም። ስፔን በ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ፈረንሳይን 2 ለ 1 ማሸነፏ አይዘነጋም።
በዚህን ውድድር የስፔን የእግር ኳስ አቅም ከአሁን በኋላ ባሉት ጨዋታዎች እንደሆነ ይገመታል።
የቡድኑ ኮከብ የሆነው ላሚን ያማል ገና ራሱን በዓለም ዋንጫ መድረስ አላስመሰከረም። የባርሴሎናው የክንፍ ተጫዋች ብቸኛ ግቡን ያስቆጠረው ከሳዑዲ አረቢያ ጋር በነበረው የምድብ ጨዋታ ነው።
በመጀመሪያዎቹ ጨዋታዎች አራት ግብ ከመረብ ያሳረፈው ሚኬል ኦያርዛባል ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ማስቆጠር አልቻለም። ስለዚህም አሰልጣን ሉዊስ ድ ላ ፉኤንቴ ከፖርቱጋል እና ቤልጂየም ጋር በነበሩት ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ጣልቃ በመግባት ሚኬል ሜሪኖን አስገብተዋል።
የ2010 የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮንነት ላይ ሌላ አሸናፊነት መደረብ የምትፈልገው ስፔኖች፤ ዛሬ ሰኞ 19 ዓመቱን የሚይዘው ያማል ተሰጥኦውን የሚገልጥ የጨዋታ ብቃት እንዲያሳይ ይጠብቃሉ።
ቁልፍ መረጃዎች - ፈረንሳይ ለግማሽ ፍጻሜ ስትደርስ ይህ ስምንተኛ ጊዜዋ ነው። ይህ ቁጥር ከብራዚል እኩል የሚያደርጋት ሲሆን ከዚህ የበለጠ ተሳትፎ ያላት 12 ጊዜ የተጫወተችው ጀርመን ናት።
በአንጻሩ ስፔን በታሪኳ ለረጅም ጊዜ ሳትሸነፍ የቆየችበት ጊዜ ላይ ናት። መጋቢት 2024 ላይ በኮሌምቢያ 1 ለ 0 ከተሸነፈች በኋላ በነበሯት 36 ግጥሚያዎች ሽንፈት አላየችም። በዚህ ጊዜ ውስጥ 27 ጊዜ ያሸነፉ ሲሆን በዘጠኙ አቻ ወጥተዋል።
ፈረንሳይ እና ስፔን ለሁለተኛ ጊዜ የሚጋጠሙበት የዓለም ዋንጫ ይሆናል። ለመጨረሻ ጊዜ ከ20 ጫእሜ በፊት በአውሮፓውያኑ 2006 በተጋጠሙበት ወቅት ፈረንሳይ ከመመራት ተነስታ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።
በድጋሚ የሚጋጠሙት ነባሮቹ ተፎካካሪዎች
ምን ይጠበቃል? - እንግሊዝ ከ2018 የዓለም ዋንጫ ወዲህ ለግማሽ ፍጻሜ ስትደርስ ይህ ሁለተኛው ነው። ነገር ግን ከ60 ዓመት በኋላ በድጋሚ የዓለም ዋንጫ አሸናፊዎቹ አርጀንቲናዎች ፊት ለፊታቸው ቆመዋል።
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በጥልቅ ስሜት እና ተቀናቃኝነት የተሞላ ነው። አሁን በድጋሚ ሜዳው ላይ የሚገናኙት አርጀንቲናዊው ኮከብ ዲዬጎ ማራዶና ብቻው በሚባል ደረጃ በሩብ ፍጻሜ ጨዋታ እንግሊዝ ግን በሜክሲኮ ከተካሄደው የዓለም ዋንጫ ውድድር ውጪ ካደረገ ከ40 ዓመት በኋላ ነው።
አሁን አርጀንቲናዎች 10 ቁጥርን የሚለብስ ሌላ ኮከብ አላቸው። ሊዮኔል ሜሲ ከእንግሊዝ ጋር ተጋጥሞ አያውቅም። የአርጀንቲና ነባር ቀናቃኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመጋፈጥ እንደ የዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ያማረ መድረክ ያለ አይመስልም።
የዓለም ዋንጫ የምንግዜውም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነትን የተቆናጠጠው ሜሲ፤ የውድድሩን የወርቅ ጫማ ለማሸነፍ በሚደረገው ፉክክር እንደ እርሱ ስምንት ግቦችን ካስቆጠረው ኪሊያም ምባፔ ጋር ይቀናቀናል።
እንግሊዞችም ግን የራሳቸው 10 ቁጥር ለባሽ ኮከብ አላቸው። ባለፉት ሁለት የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ሁለት ጊዜ ግብ ያስቆጠረው ጁድ ቢሊንግሃም፤ በአውሮፓውያኑ 1986 ወዲህ እንዲህ አይነት ስኬት ያስመዘገበ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።
የቡድኑ አምበል ሄሪ ኬን በበኩሉ በዚህ ውድድር ስድስት ግቦችን ከመረብ አሳርፏል።
በረቡዕ ዕለቱ ጨዋታ ጥልቅ ስሜት ወደተሞላበት ፍልሚያ ቢቀየር የሚያስገርም አይሆንም። የእንግሊዙ አሰልጣን ቶማስ ቱቼል የሚመሩት ደድን ኖርዌይን ባሸነፈበት የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ የበለጠ ብቃት እንዲያሳይ ሊፈልግ ይችላል።
ቁልፍ መረጃዎች - እንግሊዝ ከ2018 ወዲህ በተካሄዱ ዋና ዋና ውድድሮች አራት ግዜ ለግማሽ ፍጻሜ ደርሳለች። ከ2018 ወዲህ በነበራቸው ታሪካቸውም ለግማሽ ፍጻሜ ደረሱት አራት ጊዜ ብቻ ነው።
እንግሊዞች ከ1966 ወዲህ ለመጀሪያ ጊዜ አራት ተከታታይ የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎችን አሸንፈዋል።
አሰልጣኙ ቱቼል ኃላፊነቱን ከተረከቡ በኋላ ባካሄዷቸው የመጀመሪያዎቹ ስድስት ጨዋታዎች ያልተሸነፉ ሁለተኛው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን መሪ ናቸው። ይህንን ሪከርድ በቀዳሚነት የያዙት በ1966 ቡድኑን የመሩት አልፍ ራምሴ ናቸው።
አርጀንቲና የዘንድሮውን ጨምሮ በሦስት የዓለም ዋንጫ ውድድሮች (2014፣ 2022 እና 2026) ለግማሽ ፍጻሜ መድረስ ችለዋል። ከ1990 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለግማሽ ፍጻሜ የደረሱት በ2014 ነበር።