ከታሪካዊው የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ጀርባ ያሉ ያልተነገሩ እውነታዎች

የፎቶው ባለመብት, Reuters
የ2026ቱ የፊፋ የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያው ኳስ ከመመታቱ በፊትም አንዳንድ ታሪካዊ ሁኔታዎችን ፈጥሯል።
ይህ የዓለም ዋንጫ ከሁለት በላይ አገራት ያስተናገዱት ብቸኛው ውድድር ሲሆን፣ 48 አገራት በመሳተፋቸው ክብረ ወሰን የሆነ ውድድር ነው።
ዛሬ እሁድ ከሚካሄደው የፍፃሜ ጨዋታ በፊት በአሜሪካ፣ በካናዳ እና በሜክሲኮ በሜዳ ውስጥ እና ከሜዳ ውጪ ስለተከናወኑት ነገሮች ብዙም የማይታወቁት ክስተቶች እና ቁጥሮች የትኞቹ ናቸው?
ሊያስደንቅዎት የሚችሉ የውድድሩን አንዳንድ እውነታዎች እና ቁጥሮች እነሆ።
ስስታሞቹ ፈረንሳዮች እና ስፔናውያን

የፎቶው ባለመብት, Reuters
ስፔን በግማሽ ፍፃሜው ፈረንሳይ ለሦስተኛ ጊዜ የዓለም ዋንጫን ለማንሳት የነበራትን ፍላጎት አኮላሽታለች።
ነገር ግን ሁለቱም ቡድኖች ከፍፃሜው በፊት ባሉት ሰባት ጨዋታዎች 120 የግብ ሙከራዎችን አድርገዋል።
ዕድለ ቢሷ እንግሊዝ
በግማሽ ፍፃሜው የዋንጫ ህልሙ የተገታው ቡድን እንግሊዝ ነው። በዚህ የዓለም ዋንጫ ላይ በጣም ዕድለ ቢሱ ቡድን ሲሆን 102 ጥፋቶች (ፋውል) ተሰርተውበታል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የቡድኑ አንቀሳቃሽ ሮድሪ
የስፔን አማካይ ተጫዋች ጥሩ ለውጥ አድርጓል፤ በሰባት ጨዋታዎች ወደ 84 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ ርቀት ተጉዟል።

የፎቶው ባለመብት, Reuters
ተወንጫፊው ምባፔ
የፈረንሳዩ ኮከብ እግር ኳስ ተጫዋች በዚህ ውድድር ላይ ፈጣኑ ተጫዋች ሲሆን፣ በሩብ ፍፃሜው ሞሮኮን ባሸነፉበት ወቅት በሰዓት 37.6 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ሸፍኗል።
ሌላኛው ተጫዋች ስዊድናዊው አንቶኒ ኤላንጋ ብቻ 37 ኪሎ ሜትር በሰዓት መሮጥ በመቻል ተቀራራቢ ሰዓት አስመዝግቧል።

የፎቶው ባለመብት, Reuters
የፓራጓይ ተከላካይ እና የኪዩራሳው ክብረ ወሰን
ፓራጓይ በውድድሩ ላይ ከታዩት ታላላቅ ክስተቶች አንዱን አስመዝግባለች፤ የአራት ጊዜ የሻምፒዮናነት ክብር የነበራት ጀርመንን በ32ኛው ዙር በማሸነፍ፣ በጥሎ ማለፍ ዙር ደግሞ ተወዳጇን ፈረንሳይን ለ70 ደቂቃዎች በመገዳደር ታሪክ ሠርታለች።
ግብ ጠባቂው ኦርላንዶ ጊል በስድስት ጨዋታዎች 28 ኳሶችን በማዳን ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ይህም የውድድሩ ከፍተኛው ቁጥር ነው።
የኪዩራሳው ግብ ጠባቂ ኤሎይ ሩም በአንድ ጨዋታ 15 ኳሶችን በማዳን ስሙ በክብር የሚጠቀስ ሌላኛው በረኛ ነው።
ብሔራዊ ቡድኑ ከኢኳዶር ጋር ባደረገው ጨዋታ ግብ ሳይቆጠርበት በመደበኛው ሰዓት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ኳሶች በማዳን ክብረ ወሰኑን ተረክቧል።
የባከኑ ፍጹም ቅጣት ምቶች
በዚህ የዓለም ዋንጫ በርካታ የፍጹም ቅጣት ምቶች ተሰጥተዋል። ቁጥሩን በትክክል ለማስቀመጥ 61 ፍጼም ቅጣት ምቶች የተሰጡበት የዓለም ዋንጫ ነው።
ነገር ግን ኳስ ከመረብ የተዋሃደው በ41ዱ ብቻ ነው። ፊርም ኦፕታ የተባለው የስፖርት ተንታኝ በአውሮፓውያኑ 1966 ከተካሄደው ግጥሚያ ወዲህ ዝቅተኛ ዒላማውን የጠበቀ የቅጣት ምት የታየበት ነው ብሏል።
በዚህ ጨዋታ ሊዮኔል ሜሲ ከአንዴም ሁለቴ ፍጹም ቅጣት ምት ስቷል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
በርካታ ተጋጣሚዎች እና በካይ ጋዝ
የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ባለሙያዎች ኔትወርክ የሆነው 'ሳይንቲስትስ ፎር ግሎባል ሪሊፊኬሽን' (ኤስጂአር) በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የአየር ብክለት እንደሚኖር ይገምታል።
ባለፈው ዓመት በወጣው ሪፖርት ላይ ባለሙያዎቹ የውድድሩ የበካይ ጋዝ ልቀት ዘጠኝ ሚሊዮን ቶን ካርቦን ዳይኦክሳይድ ሊደርስ እንደሚችል ተናግረዋል፤ ይህም ካለፉት አራት የዓለም ዋንጫ ውድድሮች አማካይ በእጥፍ የሚበልጥ ነው።
ከፍተኛ ተመልካች የታደማቸው ጨዋታዎች
እንደ ፊፋ መረጃ የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ውድድር በመጀመሪያው ዙር የመጨረሻ ውድድር ላይ ከፍተኛ የተመልካቾችን ቁጥር አስመዝግቧል።
4.6 ሚሊዮን ሰዎች በ72 ጨዋታዎች ላይ መገኘት ችለዋል። ይህም በአውሮፓውያኑ 1994ቱ በአሜሪካ አስተናጋጅነት በተካሄደው ውድድር የተመዘገበውን ቁጥር የሚበልጥ ነው።
በ16ቱ ዙር መጨረሻ ላይ የተመልካቾች ቁጥር ወደ 6.25 ሚሊዮን ከፍ ብሏል። ይህም ከኬፕ ቬርዴ ሕዝብ ብዛት በ12 እጥፍ ይበልጣል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ቮዚንሃ፣ የማኅበራዊ ሚዲያ ክስተት
ስለ አፍሪካዊቷ ደሴት ኬፕ ቬርዲ እና የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ተጫዋቾች ሲነሳ የግብ ጠባቂው ቮዚንሃ ጀግንነት ወደ ማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያነት ተቀይሯል።
ወደ ዓለም ዋንጫ ሲመጣ 50 ሺህ የኢንስታግራም ተከታዮች ብቻ የነበሩት ግብ ጠባቂው የዓለም ዋንጫ በተካሄደባቸው ቀናት ውስጥ የተከታዮቹ ቁጥር ከ29 ሚሊዮን በላይ መድረሱን የገጹ መረጃ ያሳያል።
የፊላደልፊያ ከፍተኛ ሙቀት
በሰሜን አሜሪካ ያለው ከፍተኛ ሙቀት መጠን እየጨመረ በሄደበት ጊዜ ፊፋ በ2026 የዓለም ዋንጫ አስገዳጅ ፈሳሽ ለመውሰድ ፋታ የሚያገኙበት ጊዜ እንዲሰጣቸው የሚያደርግ አሠራር ጀምሯል።
ያም ሆኖ የፈረንሳይ እና የፓራጓይ ተጫዋቾች በፊላደልፊያ ስታዲየም ባካሄዱት የጥሎ ማለፍ ጨዋታ 38 ዲግሪ ሴልሺየስ የደረሰውን ሙቀት መቋቋም ነበረባቸው። ይህም እስካሁን ድረስ ያለ አየር ማቀዝቀዣ የተካሄደው ሞቃታማው ጨዋታ ነው።

የፎቶው ባለመብት, Reuters
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ያልታዩበት ውድድር
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለአገራቸው አጥቂ ፎላሪን ባሎገን የተሰጠው ቀይ ካርድ እንዲሰርዝ ፊፋን በተሳካ ሁኔታ ማግባባት እንደቻሉ ከተናገሩ በኋላ ውዝግብ ተፈጥሯል።
ሆኖም ትራምፕ እስካሁን ድረስ በውድድሩ አንድም ጨዋታ ላይ አልተገኙም።
ይህም በአስተናጋጅ አገር መሪ ዘንድ ያልተለመደ ነው። ሆኖም ግን፣ በፍጻሜው ጨዋታ ላይ እንደሚገኙ እና ዋንጫውን ለአሸናፊው ቡድን አንበል እንደሚያበረክቱ ይጠበቃል፤ የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንታኖም ይህንኑ ተናግረዋል።















